General


- የአሸዋ ኢ-ኮሜርስ መድረክ ሚስጥራዊ መረጃዎችን ለመጠበቅ እንደ ባለ ሁለት ደረጃ ማረጋገጫ ያሉ የተለያዩ
የደህንነት እርምጃዎችን ይጠቀማል። ነገር ግን እራስዎን የበለጠ ለመጠበቅ ጠንካራ የይለፍ ቃሎችን መጠቀም እና የግል
መረጃን ከማጋራት መቆጠብ አስፈላጊ ነው።

መልስ፡ አንድ ደንበኛ ከአሸዋ ገበያ ላይ ያሻውን ዕቃ ለመግዛት ሊከተላቸው የሚገቡትን ሂደቶች በሙሉ ካለፈ በኋላ
በሚመጡት የክፍያ አማራጮች ማለትም የተለያዩ ባንኮች ወይም ደግሞ ቴሌ ብርን በመጠቀም ለገዛው ዕቃ ክፍያውን በቀላሉ
መፈጸም የሚችልበት ሁኔታ ተመቻችቷል፡፡ከዚህ ባለፈ ሌሎች ጥያቄዎች ካሉ ከደንበኛ አገልግሎት ቡድን አባላት ጋር
መነጋገር እና በቂ መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

መልስ፡- አዎ! በ አሸዋ የኢ-ኮሜርስ መድረክ ላይ ሊሸጡ የሚችሉ የምርት ዓይነቶች ላይ ገደቦች አሉ። ለምሳሌ፡
መድሃኒትን፣የጦር መሳሪያዎችን በተጨማሪም አስካሪ መጠጦችን እንዲሁም ማንኛውንም ዓይነት አደንዛዥ ዕጾችን፣የወሲብ ነክ
የሆኑ ማናቸውንም ነገራት፣ምንነታቸው በግልጽ የማይታወቁ ወይም ደግሞ አወዛጋቢ የሆኑ እና በሰዎች ላይ ጉዳትን
የሚያስከትሉ ምርትና አገልግሎቶችን መሸጥ የተከለከለ ነው፡፡.

- አሸዋ ገበያ ለደንበኞቹ ቀላልና ቀልጣፋ ተደራሽነቱ የሰፋ እንዲሁም ግብይትን የሚያቀል መድረክ መሆኑ
ይታወቃል፡፡ደንበኞች ያሻቸውን ነገር ከመድረኩ ላይ ካዘዙ በኋላ የተለያዩ ትዕዛዛቸውን የሚያሰርዙ ምክንያቶች
ቢገጥሟቸው ትዕዛዛቸው ከመጋዘን ሳይወጣ ወይም ደግሞ እነሱ ጋር ሳይደርስ በፊት ትዕዛዙን መሰረዝ ወይም ከደንበኛ
አገልግሎት አባላት ጋር ተነጋግሮ ማስቀረት ይችላሉ ገንዘባቸውንም ተመላሽ የማድረግ ሙሉ መብት አላቸው፡፡ነገር ግን
ያዘዙት ዕቃ እንዲደርስላቸው ወደፈለጉት መዳረሻ ከደረሰ በኋላ ትዕዛዙን መሰረዝ አይችሉም፡፡ምን አልባት ያዘዙት እና
እነሱ ዘንድ የደረሰው ዕቃ ከተቀመጠው ዝርዝር መረጃ የተለየ ከሆነ፣በሚጓጓዝበት ወቅት ጉዳት ከደረሰበት እና የመሳሰሉት
ዕቃውን ተመላሽ ማድረግ የሚቻሉባቸው ቅድመ ሁኔታዎች ከተገኙ በ ዕቃ ተመላሽ የማድረጊያ ደንብና ግዴታዎች መሰረት
የሚታይና ተገቢው ውሳኔ የሚተላለፍ ይሆናል፡፡ከዚያ ውጭ ከሆነ (መሰረዝ በማይቻልበት ሁኔታ ትዕዛዙን ከሰረዙ )ግን
ደንበኛው የትራንስፖርት እና ሌሎች ኪሳራዎችን እንዲከፍል ይገደዳል፡፡

- አሸዋ ገበያ በመድረኩ ከሚሰጠው የተሳለጠና የተቀላጠፈ የግብይት ሂደት በተጨማሪ ደንበኞች ትዕዛዛቸውን ለመቀበል
አሸዋ ገበያ ላይ ካሉት የተለያዩ የዴሊቨሪ አማራጮች ተጠቅመው ሲያዙ እንደመረጡት የዴሊቨሪ ሁኔታ የተለያዩ የክፍያ
መጠኖች ይኖራሉ፡፡



6, ምን ያህል ደንበኛ እና ምን ያህል ሻጮች ከናንተ ጋር ኣሉ

- አሸዋ ገበያ ደንበኞች በተለያዩ አማራጮች ማለትም በ ቀጥታ ጽሁፍ ወይም በ 9870 አጭር ቁጥር በመደወል ከ
ደንበኞች አገልግሎት ቡድን አባላት ማንኛውንም ዓይነት መግዛት ከፈለጉት ዕቃ ጋር የተያያዘ ጥያቄ ማቅረብ እንዲሁም
ያሻቸውን መረጃ ማግኘት የሚችሉበት አማራጭ ዘርግቷል፡፡ስለሆነም ደንበኞች የፈለጉትን መረጃ በቀላሉ ያገኛሉ፡፡


- በሚገባ!የአሸዋ የደንበኛ አገልግሎት ቡድን አባላት ደንበኞች ግዢን ከፈጸሙም በኋላ ቢሆን የተለመደ
አብሮነታቸው እንዳለ ነው፡፡ደንበኞች በፈጸሙት ግብይት ምን ያህል ደስተኛ እንደሆኑ ለማወቅ እንዲሁም መስተካከል
ያለባቸው ጉዳዮችም ካሉ በዝርዝር አስተያየታቸውን እንዲሰጡ፣የፈለጉትን አገልግሎት እና እገዛ ማግኘታቸውን እርግጠኛ
እስኪሆኑ ድረስ በነጻነት ሃሳባቸውን እንዲያጋሩ በቀጥታ ከመደወል ጀምሮ በተለያዩ መንገዶች ያገለግሏቸዋል፡፡

- ደንበኞች ከአሸዋ የገበያ መድረክ ግብይት ሲፈጽሙ ያዘዙት ዕቃ እንዲደርስላቸው የሚፈልጉበትን አድራሻ
ይሞላሉ፡፡በተሞላው አድራሻ መሰረት የአሸዋ ዴሊቨሪ ሰራተኞች በሰዓቱ እና በቦታው ይገኛሉ፡፡ነገር ግን አንድ ሸማች
ትዕዛዙን ካስተላለፈ በኋላ እንዲደርስለት የሚፈልገበትን አድራሻ መቀየር ከፈለገ ትዕዛዙ ከመድረሱ በፊት መሆን
ይኖርበታል፡፡ ይህም የሚሆነው ለደንበኛ አገልግሎት ቡድን አባላት በአጭር ቁጥር 9870 በመደወል በማሳወቅ
ነው፡፡የአድራሻ ለውጥ የተደረገው ትዕዛዙ ከደረሰ በኋላ ከሆነ ግን የዴሊቨሪ ኪሳራውን ደንበኛው የሚሸፍን ይሆናል፡፡

- ደንበኞች በአሸዋ የገበያ መድረክ ላይ ግብይት ለመፈጸም ሲገቡ ቅናሾች(discounts) በሚለው ክፍል ውስጥ
ቅናሽ የተደረገባቸውን ምርቶች ማግኘት ይችላሉ፡፡በተጨማሪም የተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎቻችንን በመቀላቀል ሳምንታዊ
እንዲሁም የልዩ አጋጣሚ ቅናሾችን መረጃ ማግኘት እና በቅናሾቹም ተጠቃሚ መሆን ይችላሉ፡፡

- የዋስትና ሁኔታዎች እንደሚገዙት ዕቃ እና እንደ አቅራቢዎቹ ሁኔታ የሚወሰን ሲሆን አንዳንድ ምርቶች የፋብሪካ
ዋስትናን የያዙ ይሆናሉ፡፡ አንዳንዶች ደግሞ ተጨማሪ ዋስትናን ከሚያቀርቡ ሻጮች የሚገዙ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ስለሆነም
ደንበኞች በሚገዙበት ወቅት የዕቃውን ዝርዝር መረጃ በደንብ መመልከት እንዲሁም ከደንበኛ አገልግሎት ቡድን አባላት ጋር
መነጋገር እና ተያያዥ መረጃዎችን ማግኘት ተመራጭ ነው፡፡




- በሚገባ! ይችላሉ፡፡ደንበኞች ማንኛውንም አሸዋ የገበያ መድረክ ላይ የተመለከቱትን እና በአሁኑ ሰዓት ለመግዛት
ዝግጁ ሳይሆኑ ቀርተው ለወደፊት ግዢ ለማስቀመጥና ለማስታወስ የሚፈልጓቸውን ምርቶች በጋሪያቸው (cart) ውስጥ ማኖር
የሚችሉ ሲሆን ነገር ግን በጊዜ ሂደት ጋሪያቸው ውስጥ የተቀመጠው ዕቃ የዋጋ ለውጥ ሊያሳይ ወይም ከቆይታ በኋላ መግዛት
በፈለጉበት ወቅት ላይ ከመጋዘን ማለቅ ሊያጋጥም እንደሚችል ግምት ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

- ደንበኞች አሸዋ ገበያ ላይ በስህተት ትዕዛዝ ካስተላለፉ እና ግዢ ከፈጸሙ ወዲያውኑ ትዕዛዛቸውን
መሰረዝ(cancel)አለባቸው፡፡ወይም ደግሞ ከደንበኛ አገልግሎት ቡድን አባላት ጋር በጽሁፍ ወይም በ አጭር ቁጥር
9870 በመደወል መገናኘት እና የግዢ ሂደቱ ሳይጀመር በፊት ትዕዛዙን የደንበኛ ቡድን እንዲሰርዙ ወይም ደግሞ ተለዋጭ
ምርት እንዲያዙ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡

-የአሸዋ ገበያን የሚጠቀሙ ደንበኞች ለአቅራቢዎችም ሆነ ለ ምርቶቻቸው ሃሳብ፣አስተያየትና ምን ያህል ደስተኛ
እንደሆኑ ደረጃ ማስቀመጥ ይችላሉ፡፡ይህም ሌሎች ገዢዎች ስለአቅራቢው ሁኔታና ሻጩ ስለሚሰጣቸው አገልግሎቶች መረጃ
እንዲኖራቸው ከማድረጉ ባለፈ የሚያሳልፉት የግዢ ውሳኔ በዕውቀት ላይ የተመሰረተ እንዲሆን ያስችላቸዋል፡፡ይህ ደግሞ
ለአቅራቢዎቹም ሆነ ለአሸዋ ገበያ መሻሻል ያለባቸውን ጉድለቶች በማስገንዘብ በየጊዜው እድገት ያለው አገልግሎትን
ለደንበኞቻቸው እንዲያቀርቡ ያግዛል፡፡

- ማንኛውም ዓይነት አሸዋ ገበያ ላይ ከሚሸጡ አቅራቢዎች ወይም ምርትና አገልግሎታቸው ጋር የተገናኘ ጥያቄም
ሆነ ቅሬታ ያለው ደንበኛ በአሸዋ ገበያ ደንበኛ አገልግሎት በኩል ማቅረብና ለጥያቄዎቹ ምላሽ ለቅሬታዎቹም መፍትሄ
ማግኘት ይችላል፡፡

- አዎን! አሸዋ ገበያ በመድረኩ ላይ ደጋግመው ለሚገዙ ደንበኞቹ የተለያዩ ሽልማቶችና የታማኝነት ማረጋገጫ
ፕሮግራሞች አሉት፡፡ እነዚህ ፕሮግራሞች ቅናሾችን፣ነጻ ዴሊቨሪ እና ሌሎችን የሚያካትቱ ሲሆን ደንበኞች በደንበኝነታቸው
ብቻ ተጠቃሚ የሚሆኑበት፣ያሻቸውን ዕቃ መግዛት የሚችሉበትና በየቀኑ በስልካቸው በመጫወት ሳንቲሞችን የሚሰበስቡበት
በአሸዋ ገበያ መተግበሪያ ላይ የሚገኘው የ “ሼክ ኤንድ ኧርን” ጨዋታ አንዱ ማሳያ ነው፡፡


- ደንበኞች አንድን በንግድ ስም የሚያውቁትን ወይም የሚፈልጉትን ምርት ለመግዛት ሲያስቡ በቀላሉ ምርቱ የሚገኝበት
ዘርፍ( category) ውስጥ ጽፎ በመፈለግ( search በማድረግ) ማግኘት እና የግዢ ሂደቱን ተከትሎ ግብይት መፈጸም
ይችላሉ፡፡

- አሸዋ ገበያ ደንበኞቹ ወደ መድረኩ ሲገቡ አዳዲስ ምርቶችን መመልከት የሚችሉበት የራሱ (new arrivals
)የሚል ክፍል ያለው ሲሆን ሸማቾች ሁልጊዜ ይህንን ክፍል መጎብኘት እና አዲስ የገቡ ዕቃዎችን መገብየት ይችላሉ፡፡

- እንደሚታወቀው አሸዋ ገበያ በመድረኩ ላይ የሚሸጡ አቅራቢዎች በደንበኞች እንዲገመገሙ ምርትና አገልግሎታቸው ላይ
ተጠቃሚዎች ሃሳብና አስተያየት ብሎም ቅሬታቸውን መግለጽ እንዲችሉ አመቻችቷል፡፡በተጨማሪም ባላቸው የአገልግሎት ደስታ
መጠን ደረጃ መስጠትም የሚችሉበት ሁኔታ ያለ በመሆኑ አዳዲስ ደንበኞች ወደ መድረኩ በሚመጡበት ወቅት የሌሎች
ተገልጋዮችን ሃሳብ፣አስተያየት፣ቅሬታ እና የእርካታ ደረጃ መገምገሚያ ኮከቦች በመመልከት የአቅራቢውን ሁኔታ መረዳት
እንዲሁም የግዢ ውሳኔያቸውን በመረጃ ላይ የተመሰረተ ማድረግ ይችላሉ፡፡

- የጅምላ ሽያጭ ሁኔታዎች እንደአቅራቢዎቹ የሚወሰን ሲሆን ሻጮች መሸጥ የሚጀምሩበትን ብዛት በምርቱ ዝርዝር ላይ
አነስተኛ መግዛት የሚቻለው መጠን በሚለው ቦታ ያስገባሉ፡፡ደንበኞችም በተቀመጠው ዝርዝር መሰረት ማዘዝና መስተናገድ
ይችላሉ፡፡አንዳንድ አቅራቢዎች ደግሞ በተለየ ሁኔታ የጅምላ ዋጋ እና የችርቻሮ ዋጋን በልዩነት በማስቀመጥ በጅምላ
የሚገዙ ደንበኞች የተሻለ ቅናሽ የሚያገኙበትን ሁኔታ ያስቀምጣሉ፡፡በአጠቃላይ ሸማቾች አንድን ምርት ለመግዛት ሲፈልጉ
በምርቶቹ ላይ የተቀመጠውን ዝርዝር ሁኔታ መመልከት እና በሱ መሰረት ግብይታቸውን መፈጸማቸው የሚመከር ነው፡፡ከዚህ
በተለየ መልኩ ሌላ ፍላጎትና ጥያቄ ያላቸው ሸማቾች ከደንበኛ አገልግሎት ቡድን አባላት ጋር መነጋገር ይችላሉ፡፡


- አዎን! አሸዋ ገበያ የደንበኞችን ትዕዛዝ ለማድረስ የተለያዩ የዴሊቨሪ አማራጮችን የሚጠቀም ሲሆን እነዚህም
የዴሊቨሪ አማራጮች የተለያየ ዋጋ ያላቸው ናቸው፡፡ስለሆነም ሸማቾች ከአሸዋ ላይ ያሻቸውን ምርት ሲገዙ አያይዘውም
የሚፈልጉት ቀን ወይም ሰዓት ካለ መምረጥ እና በጠቀሱት ጊዜ በፍላጎታቸው መሰረት መስተናገድ ይችላሉ፡፡

Corporate Information

A.S.H.E.W.A. stands for Association Strategically for Higher and Easy-going Wealth in Africa
Our Mission is Creating the necessary conditions for business to be done easily and efficiently at any time and place and to be a credible platform and to form variety of systems to make our community’s life easier, better and more prosperous.
Currently Ashewa.com is located in Ethiopia Addis Ababa: 22 Mazoriya town square mall 8th floor House no: New office no: 803
At this time Ashewa.com it currently has a total of 12 Board members, hundreds of shareholders and 52 professional staffs.
Ashewa has increasingly expanded its Corporate Social Responsibility (CSR) efforts and prioritized building a positive social and environmental impact into its business model. Ashewa technology solutions has been participating and taking the initiative in humanitarian activities and it is a socially responsible company. Hence the main involvements in social movements are "Demén lewogené" blood donation program, "Genan ke wegené gar" humanitarian action and in helping and sponsoring social events “Ené negn Mefthew” event can be good examples.

Business Operations Information

Our customers include both buyers and sellers on our marketplaces, and they discover, select and transact with each other on our platform. Buyers and sellers access our marketplaces free of charge. Buyers include consumers who come to our retail marketplaces to shop for anything anytime anywhere, as well as business buyers who use our wholesale marketplaces to source products for use in their own business or for resale. Sellers use our marketplaces to establish a presence on the Internet and market products and services to hundreds of millions of consumers and other businesses. Sellers include brands, retailers, wholesalers and manufacturers.
An ecosystem has developed around our platforms and businesses that consist of consumers, merchants, brands, retailers, strategic alliance partners and other businesses. Ashewa technology has more than 11 sectors like E-commerce, E-learning, Logistics and shipment, E-payment/ obirr, Media and entertainment, Cloud computing, Innovation and invention center, Ashewa social, Insurance, SE Technology, AI Technology and other. Hence when we talk about our system at the nexus of this ecosystem are our technology platform, our marketplace rules and the role we play in connecting these participants to make it possible for them to discover, engage and transact with each other and manage their businesses anytime and anywhere. Much of our effort, time and energy are spent on initiatives that are for the greater good of the ecosystem and on balancing the interests of its participants. We feel a strong responsibility for the continued development of the ecosystem and we take ownership in this development. Accordingly, we refer to this as “our ecosystem.”
Our strategies include a focus on:
  • Driving user growth and engagement
  • Empowering business to facilitate digital transformation and improve operational efficiency;
  • Continuing to innovate; and
  • Creating job opportunity.

Investor Information

You can get us either in person
  • Address Town Square mall 8th-floor office no. 802, Djibouti Street 22 Mazoria, Addis Ababa, Ethiopia
Or virtually
  • Website: ashewatechnology.com
  • Ashewa Marketplace: Ashewa.com
  • Email: info@ashewa.com
  • Phone Numbers፡ +2511666311 +2511666293 +251944070860 +251976005100
  • Short Code: 9870

Seller’s Information

You prefer to sell on Ashewa.com because;
  • It is free
  • You will have easy, fast sales and reliable market place
  • You can have your own store with dashboard
  • You can manage your order
  • You will have your own report and sales analytics
  • You can have organized ready payment method and delivery
  • You will have wide range of customer traffic for your products
  • It is hustle free and we work with trust
  • You can sale your products while your physical shop is closed.
Sellers at Ashewa.com are:
  • Manufactures,
  • Whole seller,
  • Import exporters,
  • Agro processing companies ,
  • Farmers, and farmer unions,
  • Agricultural products;
  • Clothing:
  • House, Cars:
  • Motorcycles:
  • Cosmetics and personal hygiene products;
  • Computer hardware and software;
  • Construction and real estate;
  • Electrical equipment and materials;
  • Energy products, environmental goods;
  • Fashion products and accessories;
  • Food and drink;
  • Furniture, gifts, and handicrafts;
  • Health and medical products, home appliances;
  • Home and park lighting and lighting fixtures;
  • Suitcase, and bag, machine measuring and measuring equipment;
  • Mechanical goods and ordered products;
  • Rubber and plastic products;
  • Safety and security;
  • Sports and leisure, media;
  • Textiles and leather clothing;
  • Watches, jewelry and goggles, hand tools and hobbies and transportation facilities and services;
  • We have a lot of advertising options like “Cross promotion” you will promote our site while we promote your virtual shops and products for free or Vice versa
  • For pioneer sellers we will have a promotion sites on our websites /Ashewa.com and Ashewatechnology.com /
  • Sellers can promote their service product and whole shops with our brand because we have fast delivery, easy payment with trust
Currently Ashewa.com allows only single product, But we are working on and on progress to access for multiple goods

Business Operations Information

  • You prefer to buy from Ashewa.com because;
  • You will have easy, fast service and reliable market place
  • It is hustle free and we work with trust
  • You can easily manage your order
  • You will have your own report and analytics
  • You can have organized ready payment method and delivery method
  • You will have wide range choice of products, brands and sellers; and
  • You can buy products anytime while physical shop is closed.
We have different secured payment options like Telebirr, M-birr, Hello cash, Visa card, Master card, Bank bank transfer
We are working to deliver any orders in 24 hrs.
Currently Ashewa.com allows only single product, nut we are working on and on progress to access for multiple goods.

If You Have More Questions